Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Dec 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ ጎማ ከነከለመንዳሪ እና ፍላፕ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


በድጋሜ  የወጣ  የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

ጨረታ  ቁጥር  ድ/አ/ኤ/አ/ግ/ጨ/003/2017 (ሎት-1)

የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ ጎማ ከነከለመንዳሪ እና ፍላፕ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ መዝጊያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

ሎት 1

የተለያዩ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ ጎማ ከነከለመንዳሪ እና ፍላፕ

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም  4፡00 ሰዓት

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት

ብር 80,000.00

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ከላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው::
  3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት-1 ብር 800.00 (ስምንት መቶ) የማይመለስ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. አድራሻ፡-ድሬዳዋ ግሪክ ካንፕ የድሬዳዋ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የድሬዳዋ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ግዥ፣ ሎጀስቲክስ፣ ዌርሀውሲንግ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 206/207 በአካል ቀርቦ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለስድስት ወራት የሚያገለግል የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል ‹‹ኦሪጅናል እና ኮፒ›› እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ድ/አ/ኤ/አ/ግ/ጨ/003/2017 ሎት-1 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል
  8. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 025-211-00-23/025-112-98-45 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 206/207 በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የድሬዳዋ  አስተዳደር  ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Save Tender