በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራ ሙላታ ዲስትሪክት እና ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ቦቶር በቾ ዲስትሪክ ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ እንዲሁም በባሌ ቅ/ጽ/ቤት አሎሼ ባቱ ዲስትሪከት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU-05/2017 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራ ሙላታ ዲስትሪክት እና ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ቦቶር በቾ ዲስትሪክ ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ እንዲሁም በባሌ ቅ/ጽ/ቤት አሎሼ ባቱ ዲስትሪከት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ቦሬ እና አዶላ ዲስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና TIN Number ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ጂማ ከተማ፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ ቤት ጭሮ ከተማ እና በሌ ቅ/ጽ/ቤት ጎባ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲቆይ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ደግሞ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክከለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
