በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች በሎት-01 የጽህፈት መሳሪያ በሎት-02 ኤሌክትሮኒክስ በሎት-03 ሞተር ሳይክል በሎት-04 ፈርኒቸር በሎት-05 ደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን/በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች በሎት-01 የጽህፈት መሳሪያ በሎት-02 ኤሌክትሮኒክስ በሎት-03 ሞተር ሳይክል በሎት-04 ፈርኒቸር በሎት-05 ደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የስራ ፍቃድ፤
- የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/የቲን ተመዝጋቢ የሆን፣
- አግባብነት ያለውን የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን/ በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል ግዢ ክፍል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መወዳደር ይቻላል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም ስማቸውን፤ ፈርማቸውን እና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት የሚችሉት በመ/ቤታችን በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰድላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ሁለት የኦርጅናሉ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ CPO በኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ያስያዙት CPO ለወደቁት ሲመለስ ለአሸናፊዎች ግን ዕቃውን አቅርበው ሲጨርሱ ይመለሳል ::
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የዕቃውን ናሙና አቅርቦ ተፈትሾና ተረጋግጦ በናሙናው መሰረት ዕቃው አርጅናል ብቻ ሲሆን ማቅረብ የሚችል ይሆናል::
- የጨረታ ስራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሸጊያ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የጨረታ ስነ-ስርዓት ማወክና መረበሽ ከውድድር ውጪ ያደርጋል ፤በህግም ያስቀጣል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ም/ኢ/ህ/ከ/መንግስት በካፋ ዞን በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት የስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ዕቃውን ለሚያቀርበው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO አይመስልም።
- የዕቃው የመጨረሻ ርክክብ የሚፈጸመው ጨረታው በተካሄደበት በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ጊቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥር፡- 0473380451/59
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡- በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ስነ ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን/በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
