በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ ፤ የፈርኒቸር ፤ የኤሌክትሮኒክስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የእንስሳት መድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ እና የሞተር ሣይክል ግዥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ ፤ የፈርኒቸር ፤ የኤሌክትሮኒክስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የእንስሳት መድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ እና የሞተር ሣይክል ግዥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ፡- በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ እና ለእንስሳት መድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ግዥ ሌሎች ፍቃዶች እንዳሉ ሆነው በዘር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል :: ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የጂ/ከ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ 300 / ሶስት መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል ::
ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንቶች ኦርጅናሉን ከኦርጅናሉ ጋር ኮፒውን ከኮፒው ጋር በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል :: ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን /የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ፣ የኤሌክትሮኒክስ 10,000 /አስር ሺህ ብር / የፈርኒቸር 10,000 ፣ የመኪና መለዋወጫ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ፣ የሞተር ሣይክል 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የእንስሳት መድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ 6,000 /ስድስት ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው :: አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፋባቸው ስራ ለመፈፀም ያሸነፈበት ገንዘብ 10% ሲያሲዝ ከመ/ቤቱ ጋር ሙሉ ይፈራረማሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በማግስቱ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4:30 ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ : መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አይስተጓጎልም::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር -- 0467750256 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በኣሪ ዞን የጂ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት
