የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሩዝ መፈልፈያ ኮምባይን ሀርቨስተር ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር : ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/03/2017
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሩዝ መፈልፈያ ኮምባይን ሀርቨስተር ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ሀጋዊ የ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታከስ ከሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሂ.ቁጥር 100057735167 በመከፈልና የባንከ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው::
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ካሳንቺስ ከመናኸሪያ ሆቴል ወደ አቧሬ አቅጣጫ
በሚወስደው አስፋልት መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ በማለት የቀድሞው
ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ
ስልከ ቁጥር 011 5-586725
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው::
- ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መጃ በስልከ ቁጥር 011558-62-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
