የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተሸከርካሪ ሞተር በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር ECC JB13/2017
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተሸከርካሪ ሞተር በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ሞተሩ ቀረጥ ተከፍሎበት የገባ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ዲክላራሲዮን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሣ ሺ) ብር በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በንግድ ባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ከሚገኘው ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ለየብቻ ከአንድ ኮፒ ጋር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላል
- ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀን አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ከሚገኘው ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ጨረታው ይከፈታል 16ኛ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል
- አሸናፊው ድርጅት የተሸከርካሪ ሞተሩን በራሱ ትራንስፖርት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ከሚገኘው ጉምሩከ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት አምጥቶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፤
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን ፤ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን
1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 05 መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0904252386 ወይም
0921822252-0910208950
E-mail addres jijccarchive@gmail.com
Getachewtak1@gmail.com
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
