Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Nov 2024, 9:45 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ሞባይሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ሞባይሎች  በ11/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ሞባይሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ሞባይሎች  በ11/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም  በጨረታው  ላይ  ለመካፈል  የምትልጉ  ተጫራቾች ፡-

  1. ለግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ሞባይሎቹን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5% ሲፒኦ) (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  4. ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ሞባይሎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆኑን አለበት፤
  5. ሞባይሎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው (ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፤
  6. በጨረታው ያላሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  8. ማንኛውም ተጫራች ሞባይሎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፣
  9. ተጫራቹ ሞባይሎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም
  10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ በ14/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው 3:45 ተዘግቶ በ14/03/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆናል፤

N.B - አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፈል መሆኑ ይታወቅ፣ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡

 

የጉምሩክ  ኮሚሽን  ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender