Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ
  • Address ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057 661 17 31
  • Website
  • Deadline04 Dec 2024, 4:40 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በአሮሚያ ከልል ጤና ቢሮ የነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ ለሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአሮሚያ ከልል ጤና ቢሮ የነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም

  1. የጽህፈት መሣሪያዎች
  2. የጽዳት ዕቃዎች
  3. የቢሮ ዕቃዎች
  4. የኮምፒዩተር ዕቃዎች
  5. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  6. የህክምና ዕቃዎች
  7. የቢሮ ፈርኒቸሮች
  8. የተሽከርካሪና የሞተር ብስክሌት ጎማዎች
  9. የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ  የሚከተሉትን  መስፈርቶች  የምታሟሉ  ተጫራቾች  በጨረታው  እንድትሳተፉ  እንጋብዛለን።

  1. በዘርፉ ላይ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ያለው።
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. የቫት ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ ::
  5. ቲን ያለውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።
  6. በአቅራቢነት መመዝገቡን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  7. ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት ።
  8. የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን ሠነድ መግዛት ይችላል
  9. ያሸነፉትን ዕቃ በራሣቸው ወጪ እስከ ነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ በኮሚቴ ታይቶ ተቀባይነት ካጣ ኮሌጁ የመመለስ መብት አለው።
  12. ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው የአንዱ ዕቃ ዋጋ ላይ ቫት ጨምሮ ሠርቶ ማቅረብ አለበት ያለቫት ተሠርቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
  13. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ጨረታውን መተው ወይም ሌላ ሃሣብ ማቅረብ አይችሉም።
  14. ኮሌጁ ባቀረበው ሠነድ ላይ መሠረዝ መጨመር አይቻልም ። ስርዝ ድልዝ ያለው ዋጋ ተቀባይነት የለውም ።
  15. ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ብር ሃያ አምስት ሺህ ) ለውል ማስከበሪያ የግዥ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለበት ከባንክ በተረጋገጠ CPO ውጪ ማንኛውም ማስያዣ ተቀባይነት የለውም ።
  16. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ማንኛውም ተጫራች መንግስት ከሚያወጣው ጨረታ ውጪ ይሆናል።
  17. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
  18. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መቀበል አለበት።
  19. ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ ዋጋውን ከሞሉ በኋላ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ለእያንዳንዱ ጨረታ በዋናና በኮፒ በሁለት ኤንቨሎፕ በሰም ታሽጎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  20. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አሥራ አምስት) ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል ። ነገር ግን ቀኑ ዓመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  21. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

     ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 057 661 17 31 ነው።

 

በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የነቀምቴ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ

Save Tender