በበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያየ በሎት ምድብ የተከፋፈለ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የ2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግል መለያ ቁጥር አበበች /ጎበና/የመ/ደ/ት/ቤት 02/2017 ዓ.ም
አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያየ በሎት ምድብ የተከፋፈለ እቃዎችን ማለትም:.
ሎት 1 የደንብ ልብስ
ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
ሎት 3 አላቂ የህከምና እቃዎች
ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች
ሎት 5 አላቂ የፅዳት እቃዎች
ሎት 6 ዝቅተኛ ቋሚ እቃዎች
ሎት 7 ቋሚ ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ደኖርባችኋል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅ የግዥ የግልጽ ጨረታን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከ9/03/2017 ጀምሮ እስከ 20/03/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን 2% በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀው ሲፒኦ ከኦርጅናል ማስረጃ ፖስታ ውስጥ ሲፒኦ በማድረግ በመያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶቻቸው ጋር ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ የውል ማስከበሪያ የሚሆን ያሸነፉበት የገንዘብ መጠን 10% ሲፒኦ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለውል ማስከበሪያ አያገለግልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት በአበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሰነዶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማህተም በማድረግ በታሸገ ካኪ ፖስታ ሳጥን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ23/03/2017 ዓ.ም በ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ስአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው አምራችና የአገር ውስጥ ምርት የሚያቀርቡ ከሆኑ ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ እኛ ሰነድ ለመወሰድ ስትመጡ አምራች ስለመሆናችሁና የአገር ውስጥ ምርት መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን አምራችና የአገር ውስጥ ምርት አቅራቢ ካልሆናችሁ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ መግዛትና ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባችኋል። በተጨማሪ መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ባዘጋጀነው ሰነድ ነው ሞልቶ ማቅረብ የሚቻለው ከዚያ ውጪ ለሚያመጣ ውድቅ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን ሰነዱን ሙሉ ለሙሉ መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ የግዢ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፡- ዮሐንስ ጸበል አካበቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ በሚያስገባው ወይም በተለምዶ አይሻ መስጊድ አጠገብ
ስልከ ቁጥር ፡- 0118126317
አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
