Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
  • Address ሀዋሳ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 135 0012
  • Website
  • Deadline29 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር ተ/አገ/ለኮሌጁ የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር ተ/አገ/ለኮሌጁ የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌደራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፤ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ Website ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 10,000 (አስር ሺህ) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በተቋሙ አካውንት 1000053091443 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የውስጥ ገቢ ስም በማስገባት እና እስሊፕ በመያዝ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ (ይ/ዓለም) ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም ቢሮ ቁጥር 26 ቀርበው መግዛት ይችላሉ። ጨረታው የሚወጣበት 9/3/2017 ዓ.ም ጨረታው የሚከፈትበት 23/3/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 23/3/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም

ስልክ ቁጥር ፡- 0461350012

 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ

Save Tender