Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የሞላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0116220730
  • Website
  • Deadline03 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ግዥዎችን መግዛት ስለፈለገ ማለትም ሎተ1፡- የፅህፈት መሳሪያ ሎት2፡- ጎማና ከነመዳሪ፤ ሎት3፡- ደንብ ልብስ፤ ሎት4፡- የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የሞላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ግዥዎችን መግዛት ስለፈለገ ማለትም ሎተ1፡- የፅህፈት መሳሪያ ሎት2፡- ጎማና ከነመዳሪ፤ ሎት3፡- ደንብ ልብስ፤ ሎት4፡- የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፤
  2. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው/ያላት፤
  3. የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ች፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚቀርቡ አቅርቦቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዝቅተኛ ዋጋውን የሞላ ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የውድድር አይነት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በሞላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዋና ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 69 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ሰነዱን በመሙላት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን በጥንቃቄ በተዘጋጀው ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 69 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላእ የሚከፈት ሲሆን ነገርግን ቀኑ በዓል፤ እሁድ ቅዳሜ ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት።
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ፈጽሞ እቃውን በሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል/ ይኖርባታል።
  11. በጨረታ ያላሸነፉ ተጫራቾች አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የጨረታው ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0116220730/0116220609 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአብክመ  ሰሜን  ሸዋ  ዞን  መንዝ  ማማ  ምድር  ወረዳ  የሞላሌ  የመጀመሪያ  ደረጃ  ሆስፒታል

Save Tender