ድርጅታችን ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የTOR For Conducting External Customer Satisfaction Survey and Market Assessment የደንበኛ እርካታና የገበያ ዳሰሳ ጥናት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 035/2017 ዓ.ም
ድርጅታችን ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የTOR For Conducting External Customer Satisfaction Survey and Market Assessment የደንበኛ እርካታና የገበያ ዳሰሳ ጥናት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- የታደሰ ፈቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- የማይመለስ ቫትን አካቶ ብር 120.00 /አንድ መቶ ሃያ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት።
- ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ታኅሣሥ 3/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡10 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፖ.ሣ.ቁ. 3516 ስልክ 011 369 0563 ፋክስ 011 369 0563
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
