Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
  • Address , Phone: 011-662-90-15
  • Website
  • Deadline17 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

ኬሚካል ኢንዲስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1. የእስቴሽነሪ ዕቃዎችን እና ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

  የጨረታ ቁጥር ኬ.ኢ.ኮ/ግ/ጨ/04-2017

ኬሚካል ኢንዲስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ

          ሎት 1. የእስቴሽነሪ ዕቃዎችን

          ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎችን

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግበር የከፈሉበት፤ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለሰላሳ (30) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሀኖ ይቆያል። ስለሆነም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ያዘጋጁትን የጨረታ ሠነድ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 የማይመለስ ብር አንድ መቶ ሃምሳ (ብር 150.00) በመክፈል ቦሌ አካባቢ ፍሬንድ ሺፕ ህንፃ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋነ መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ የኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል። የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም። 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል።
  4. ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ ለይተው በተለያየ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን ስም ለጨረታ ያቀረቡትን ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በባንክ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን

Save Tender