በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን፤ የደንብ ልብሶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሱሉልታ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን፤ የደንብ ልብሶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኣላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና /TIN/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ለዚሁም የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች መካፈል ይችላሉ።
- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የግብር ከፋይ ክሊራንስ እና የ2016 ዓ.ም ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት እቃ ናሙና (sample) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በ21ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- በ21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱን እስከ 4፡00 ተዘግቶ ወዲያው 4፡30 የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ይመለሳል።
- ለጨረታ የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ ሁሉንም እቃዎችን ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰው ዋጋ የጨረታው ሂደት አልቆ ርክክብ እስከሚደረግ ድረስ ዋጋው የፀና ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊዎች የአሸነፉበትን እቃዎች በጠቅላላ በራሳቸው ትራንስፓርት አምጥተው ዕቃ ግምጃ ቤት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0914990505/0921801813 / በመደወል ወይም በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግዥ ክፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሱሉልታ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
