በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ አጠቃላይ የመ/ቤቱን ዋና ዋና ሥራዎችን ለማስተዋወቅ ይረዳ ዘንድ ደረጃቸውን የጠበቁ አራት (4) የተለያዩ ቢል ቦርዶችን ከአዲስ አበባ - አዳማ ፤ ሞጆ ባቱ እና በተመሳሳይ ሁኔታ አዳማ - አዲስ አበባ እና ባቱ - ሞጆ የፍጥነት መንገድ ላይ በሚገኙ ክፍት የማስታወቂያ ቦታዎች ላይ ደርጅቱ ባዘጋጀው የቦታ ይዘትና የጥራት ደረጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Buusaa Gonolaa Microfinance S.C (ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር BGO 02/2017
ቢል ቦርድ ለማሰራት በድጋሜ የወጣ ግልጽ ጨረታ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ አጠቃላይ የመ/ቤቱን ዋና ዋና ሥራዎችን ለማስተዋወቅ ይረዳ ዘንድ ደረጃቸውን የጠበቁ አራት (4) የተለያዩ ቢል ቦርዶችን ከአዲስ አበባ - አዳማ ፤ ሞጆ ባቱ እና በተመሳሳይ ሁኔታ አዳማ - አዲስ አበባ እና ባቱ - ሞጆ የፍጥነት መንገድ ላይ በሚገኙ ክፍት የማስታወቂያ ቦታዎች ላይ ደርጅቱ ባዘጋጀው የቦታ ይዘትና የጥራት ደረጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
- ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ፤ የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ ከቢሮ ቁጥር 20 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዶቹን ዋናውን ቅጂውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 20 ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዶቹን ዋና እና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 21 ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳትን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሀን ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ (አርባ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል።
- ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በቅድሚያ ያሲይዛሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 251 11 4709028 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ ፡- ሳሪስ አዲስ ጎማ/ሆራይዘን/ፋብሪካ ፊት ለፊት
ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ
