Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያዎችና የጽዳት እቃዎች፣ ለሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ ስራ ልብስ፣ የጫማና የቆዳ ውጤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

  የግዥ  መለያ  ቁጥር  001-003/2017

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያዎችና የጽዳት እቃዎች፣ ለሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ ስራ ልብስ፣ የጫማና የቆዳ ውጤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

እያንዳንዱ የጨረታ ተካፋይ የሚከተሉትን ጨረታ መመሪያ ነጥቦች በግልጽ በመረዳት በጨረታ ሰነዶች ላይ እንዲሟላ ማድረግ አለበት።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቅ/ጽ/ቤቱ በ3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 310 ገንዘብ ቤት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሕዳር 24/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የሚጫረቱበትን ምድብ (ሎት) እንዲሁም ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው ሳጥን ከሕዳር 09/2017 ዓ.ም እስከ ሕዳር 23/2017 ዓ.ም ድረስ ቆይቶ በማግስቱ በሕዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች በቴክኒካል የጨረታ ሰነዳቸውን አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው።
    1. ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ እንዲሁም VAT (የተጨማሪ እሴት ታክስ) እና TIN (ግብር ከፋይ ምዝገባ ም/ወረቀት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የኦርጅናል ኮፒ መረጃ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ግብርና ታክስ ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ሲሆን፤ በእርሳስ ተሞልቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ላይ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ የባለስልጣኑ (የድርጅቱ ባለቤት /ተወካይ/ ፊርማ የሌለበት ከሆነ ለአቅርቦቱ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
  8. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ከዚህ በታች በተጠቀሰው የብር መጠን መሰረት ገቢዎች ሚኒስቴር ድ/ዳ/ቅ ጽ/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ CPO አልያም ደግሞ በጥሬ ገንዘብ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ወይም የክፍያ ትእዛዝ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ዝርዝር ውስጥ በተጫራቹ ምርጫ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

ተ.ቁ

የእቃው ዓይነት

የገንዘብ መጠን

ሎት 1

የጽሕፈት መሳሪያዎች

10,000.00

ሎት 2

የጽዳት እቃዎች

25,000.00

ሎት 3

የደንብ ልብስ

10,000.00

  1. መ/ቤቱ የተጫራቾችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መስፈርቶች የጨረታ መመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያካተተ ስለሆነ ሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾች እንዲተገብሩ ያሳስባል።
  2. ተጫራቾች ስለ ማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈፀም ማረጋገጫ በመስጠት ግዴታ የሚገባበትን ቅጽ በመፈረም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 025-411-65-51 ድሬዳዋ ገቢዎች ሚኒስቴር ግዢና ፋይናንስ አስተዳደር በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender