የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሰራተኞች መኖሪያ ግቢ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- EEP/GOP/NCB/08/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሰራተኞች መኖሪያ ግቢ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲኒያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ መምሪያ ህንጻ ምድር ቤት ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጥበቃ አገልግሎት በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/08/2017 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 1 (አንድ) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሰንጠረዥ መሰረት ለ90 ቀናት የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንከ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
የግዥው ዓይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
|
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
|
የጥበቃ አገልግሎት
|
ብር 10,000.00
|
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት
|
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት
|
* ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
• ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5-57-42-95 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
