የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የጽሕፈት መሳሪያዎችና የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ብሎ/003/2017
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የጽሕፈት መሳሪያዎችና የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር መሠረት፡-
ሎት 1፡- የጽሕፈት መሳሪያ ዕቃዎች
ሎት 2፡- የጽዳት መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ሎት1 ላይ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም ሎት 2 ላይ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ ያለባቸው ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገው ዋናው ደረሰኝ ማያያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርኘራይዝ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ የተደራጁ ህጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ ያለባቸው ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ጨረታ የሚወዳደሩበት ተቋም ስም፣ የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ መለያ ቁጥርና የጨረታ ማስከበሪያውን የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሊራስ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የምስከር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል “ሚገባበት ቅፅ ሞልተው ከመጫረቻ ሠነዶቻቸውና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አስተዳደሩ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
