Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ
  • Address ወላይታ ሀገር : ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለተኛው መግቢያ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) በስተጀርባ ከሚገኘው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0461801798
  • Website
  • Deadline01 Dec 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በወላይታ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያሠራቸው ግንባታ ሥራዎች የግንባታ ጥሬ ዕቃ የጥርብ ድንጋይ፣ የክስካሶ ድንጋይ፣ አሸዋ እና ጠጠር ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በወላይታ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያሠራቸው ግንባታ ሥራዎች የግንባታ ጥሬ ዕቃ የጥርብ ድንጋይ፣ የክስካሶ ድንጋይ፣ አሸዋ እና ጠጠር ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህም  መሠረት  በጨረታው  መሳተፍ  የሚፈልጉ  ተጫራቾች  ማሟላት /ማቅረብ  ያለባቸው

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
  2. ለ2017 ዓ.ም. የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፤
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
  5. ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ሕጋዊ ታክስ ክሊራንስ፣
  6. የጨረታ ማስከበርያ በካሽ ወይም በCPO ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) ማቅረብ የሚችል፤
  7. የግንባታ ግብአቶችን ወደ ሳይት በተፈለገው ጊዜ በሚፈለገው ጥራትና መጠን ማቅረብ የሚችል፤
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለተኛው መግቢያ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ መምህራን መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) በስተጀርባ ከሚገኘው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጥሬ ዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያና ቴከኒካል ሰነድ ዋናውን (ኦሪጅናሉን) አንድ ላይ በማሸግ እና የዋጋ  ማቅረቢያና ቴክኒካል ሰነድ አንድ አንድ ኮፒ በሌላ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጻፍ እና ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ከፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
  11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0461801798 /0461801509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።  

አድራሻ፡- ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለተኛው መግቢያ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) በስተጀርባ ከሚገኘው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት

 

በወላይታ  ልማት  ማህበር  ዳሞታ  ኮንስትራክሽን  ኩባንያ

Save Tender