በትምህርትና በስልጠና ዋና መምሪያ የወታደራዊ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ለክፍሉ አገልግሎት የሚሰጡ የፅህፈት ዕቃዎች ፤ የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የቤቶች ቀላል ጥገና ዕቃዎችን ለመግዛት በሎት አዘጋጅቶ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል።
በትምህርትና በስልጠና ዋና መምሪያ የወታደራዊ ኮሌጅ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ወ/መ/ኮ/ግ/ጨ/002/2017
በትምህርትና በስልጠና ዋና መምሪያ የወታደራዊ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ለክፍሉ አገልግሎት የሚሰጡ የፅህፈት ዕቃዎች ፤ የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የቤቶች ቀላል ጥገና ዕቃዎችን ለመግዛት በሎት አዘጋጅቶ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የፅህፈት ዕቃዎች እና የትምህርት መርጃ ዕቃዎች
ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3 የቤቶች ቀላል ጥገና ዕቃዎች
በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት (ኦላይን)
- የቫት/ተጨማሪ እሴት ታክስ/
- የቲን ነምበር ሰርተፍኬት
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ምስክር ወረቀትና
- የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡና ዋናውን ሲጠየቁ ማሳየት የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ሥነ-ሥረዓትና ይህንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊከ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ይሆናል፡
- ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ለያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፤፤ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን
ሎት 1. የፅህፈት ዕቃዎች እና የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ ብር 12,000 ብር
ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች 7500 ብር
ሎት 3. የቤቶች ቀላል ጥገና ዕቃዎች 5,200 ብር ብቻ በወታደራዊ መረጃ ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የፋይናንስ ተቋማት/ባንኮች/ CPO አሰርቶ ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ካደራጃቸው ህጋዊ ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ሰነዱ ወጪ የሚሆንበትን የምታገኙት ቢሮ ቁጥር 35 እና ጨረታው የሚከፈትበት አዳራሽ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ክ/ከተማ ሜታ አቦ ወረዳ የወታደራዊ ኮሌጅ - ሜታ ቢራ ፋብሪካ አጠገብ ይገኛል ስልክ ቁጥር 0914-15-23- 89 /0920-05-56-90
በትምህርትና በስልጠና ዋና መምሪያ የወታደራዊ ኮሌጅ
