Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) (የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address Gurd Shola, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011 8-96-29-91
  • Websitehttp://ecwc.gov.et/
  • Deadline27 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) (የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ  ጥሪ  ማስታወቂያ

     የጨረታ  ቁጥር  ECWCT/NCB/SG-41/2017

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ለድርጅቶች የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሲሆን ለግለሰብ ደግሞ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚመጣ ተዛማጅ የሆነ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
  3. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ተጫራች ክፍት ነው። የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንከ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ አንድ ቢሮ

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ስትሴቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ

አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር:- 0118 72 29 91/ 011872 29 58

 

የኢትዮጵያ  ኮንስትራክሽን  ሥራዎች  ኮርፖሬሽን

 

Save Tender