Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
  • Address ሀዋሳ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 135 0012
  • Website
  • Deadline21 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር ተ/አገ/ ለኮሌጁ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ

የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር ተ/አገ/ ለኮሌጁ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግሥት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣
  2. በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ /Website /ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ወይም የባንከ ጋራንቲ የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በተቋሙ አካውንት 1000053091443 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የውስጥ ገቢ ስም በማስገባት እና ስሊፕ በመያዝ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ (ይ/ዓለም) ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም ቢሮ ቁጥር 26 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚወጣበት ኅዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጨረታው የሚከፈትበት ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ነው፡፡
  5. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኤ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ግዥና  ንብረት  አስተዳደር  ቲም

ስልክ ቁጥር፡- 046 135 0012

 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ. ኮሌጅ

Save Tender