የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ Lot 1. ኤሌክትሮኒክስ (Electronics) Lot 2. Furnitures /ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች Lot 3. Stationaire / አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ Lot 1. ኤሌክትሮኒክስ (Electronics) Lot 2. Furnitures /ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች Lot 3. Stationaire / አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ድርጅቶች፣
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በመንግስት ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከዚህ በፊት በመስኩ አገልግሎት የሰጡበትን የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ከመንግስታዊ መ/ቤት ወይም ተቋማትና ከሌሎች ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በቢሮው ስም አዘጋጅተው ማቅረብ የሚችሉ፣
- እንደአስፈለጊነቱ በጨረታው የሚሣተፉ ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ቢሮው ናሙና እንዲያቀርቡ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ቴከኒካልና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውንና ስልክ ቁጥራቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ አንስቶ አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በመቁጠር እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብ/ክ/መ/ል ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሠነዱን ማስገባት ይቻላል፡፡
- ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት አሸናፊ ሲሆኑ ለሚያቀርቡት ዕቃ ከጥራት ጋር ተያይዞ ለሚቀርቡ ሀሣቦች ሙሉ ኃላፊነት (የጥራት ዋስትና) ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው 400 ( አራት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ ይህ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሲዳማ ብ/ክ/መ/መ/ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
