በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት ሎት 1፡-አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃ፣ ሎት 2፡-የደንብ ልብስ ፣ ሎት 3፡- የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች ፣ ሎት 4፡- የሰራተኛ መታወቂያ ፣ የደረት ባጅና የጠረጴዛ ቴፕሌት ህትመት እና ሎት 5፡- የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- አ.አ.ቤ.ል.ኮ.ም/ቅ/ጽ/ቤት/002/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት
ሎት 1፡-አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃ፣ ሎት 2፡-የደንብ ልብስ ፣ ሎት 3፡- የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች ፣ ሎት 4፡- የሰራተኛ መታወቂያ ፣ የደረት ባጅና የጠረጴዛ ቴፕሌት ህትመት እና ሎት 5፡- የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት/ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡ የኢንሹራንስ ዋስትና ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከቅ/ጽ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ በአ/አ/ከ/ አስ/ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ/ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ላይ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በግልጽ ስለሚቀመጥ መመልከት ይቻላል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ በሻሌ 40/60 ኮንዶሚንየም ውሃ ታንከር አካባቢ ብሎክ 13 ፊት ለፊት ስልከ ቁጥር፡- 0911-06-33-70 እና 0913-48-96-63
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት
