በሰመራ ሎገያ ከተማ መስተዳድር በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የግራኒፊኬሽን ስራ በያዘው በጀት መሰረት በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሎግያ ከተማ መስ/ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሰመራ ሎገያ ከተማ መስተዳድር በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የግራኒፊኬሽን ስራ በያዘው በጀት መሰረት በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች በማሟላት መወዳር የምትችሉ ሲሆን፣-
- ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም-
-
- ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤
- የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፊኬት ያለው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( TIN ) ሰርትፊኬት ያለው፤
- የጨረታ ሰነድ ግዥ መፈጸም
- በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
-
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የሰመራ ሎግያ ከተማ መስተዳድር ፋይ/ኢኮ/ጽ/ቤት ውስጥ የግዥና ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በእያንዳዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከማንኛውም ተጫራቾች የሚቀርብን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 5/3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም ህዳር 20/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን የሚዘጋ ሆኖ በእለቱ ከግማሸ ሰዓት በኋላ 4:30 በከንቲባው ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/የስራ ሂደት ክፍል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በቢሮችን በአካል በመቅረብ ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 033 666 0583 ደውሎው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሎግያ ከተማ መስ/ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
