Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዑፋ ጤና ጣቢያ
  • Address በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዑፋ ጤና ጣቢያ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 047-2-22-04-90
  • Website
  • Deadline05 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዑፋ ጤና ጣቢያ ማስፋፍያ የተመላላሽ ታካሚ እና ተኝቶ ታካሚ ከፍል ግንባታ በዑፋ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በ2017 ዓ.ም በካፒታል በጀት ሥራ እንዲሠራላቸው ከመ/ቤታቸው በቁጥር 2504/07-127/ በቀን 27/02/2017 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዑፋ ጤና ጣቢያ


ለመጀመሪያ  ጊዜ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር፡- 2

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዑፋ ጤና ጣቢያ ማስፋፍያ የተመላላሽ ታካሚ እና ተኝቶ ታካሚ ክፍል ግንባታ በዑፋ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በ2017 ዓ.ም በካፒታል በጀት ሥራ እንዲሠራላቸው ከመ/ቤታቸው በቁጥር 2504/07-127/ በቀን 27/02/2017 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ፡-

  • የጨረታው አይነት፡- ግልጽ ጨረታ
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው፤
  • የተጫራቹ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ GC-5/ BC-5 (ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭ)
  • ተቋራጩ በከፋ ዞን በኩል ውል ገብቶ ግንባታ እያከናወነ ከሆነ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከካፋ ዞን ከተ/ል/ኮን መምሪያ ማቅረብ የሚችል እና ውል ያላቋረጠ፤
  • በእጃቸው ሥራ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ስራው የደረሰበት ደረጃ 80% እና ከዚያ በላይ ለመሆኑ ማረጋገጫ ደብዳቤ ከተቆጣጣሪ መ/ቤትና ከአሰሪ ተቋም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታውን ሠነድ ከጊምቦ ወረዳ ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው የማይመለሰ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የገዙት የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ በመሙላት ቴክኒካሉን አንድ ኦሪጂናል ከሁለት ኮፒ ጋር ፋይናንሻሉንም አንድ ኦሪጅናል ከሁለት ኮፒዎች ጋር በተናጠል በእናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ጨረታው ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ22 ተኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ሲሆን ታሽጎ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ በተዘረዘረው መጠይቅ መሠረት ዋጋውን ሞልተው በመፈረምና ህጋዊ የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ገጽ ማሳረፍ አለባቸው፡፡
  • አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ከአሰሪው መ/ቤት ጋር ውል መግባት አለበት፡፡
  • ጨረታው የሚታሸግበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም ከስራ ቀን ውጭ ከሆን በሚቀጥለው የስራ ቀንና በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር : - 047-2-22-04-90/055 ይደውሉ።

 

በደቡብ  ምዕራብ  ኢትዮጵያ  ህዝቦች  ክልላዊ  መንግሥት  በካፋ  ዞን  ጊምቦ  ወረዳ  ዑፋ  ጤና  ጣቢያ

Save Tender