Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Nov 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Maintenance And Repair

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመከራየት ይፈልጋል፡፡


  የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር 26

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን

ሎት 1 የውሃ ትራንስፖርት (በቦቴ) ለመከራየት፣

ሎት 2 የመኪና ጎማዎች ለመግዛት፤

ሎት 3 የዱር እንስሳት ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ለመግዛት፤

ሎት 4 የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶኮፒ ጥገና ሥራ ለአንድ ዓመት ውል በማሰር፣

ሎት 5፡- የተለያዩ መኪናዎችን ሰርቪስና ጥገና ለማስደረግ የአንድ ዓመት ውል በማሰር ለማሠራት፣

ሎት 6 የኪዌስክ አገልግሎት የአንድ ዓመት ውል በማሰር ለማሠራት፡

ሎት 7 የተለያዩ ማሽነሪዎችና ፓምፖች ጥገና ፣ ቢሮዎችን ቀለም መቀባትና የቢሮ ፈርኒቸሮችን መጠገን ሥራ ውል በማሰር፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሺያል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶከመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ በአራት ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ በግዥና ንብረት ዳይሬከቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

ስልክ ቁጥር 0115572917/ 0115572949 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር  የሕዝብ  መዝናኛ  ቦታዎች

አስተዳደር  ኮርፖሬሽን

Save Tender