የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን መሪ የ2017 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
አመድ ጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን መሪ የ2017 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የፅ/መሳሪያዎች
- የቢሮ የፅዳት ዕቃዎች፡
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ (አልባሳት)
- የህንፃ መሳሪያዎች እና የመኪና ጎማ ፣ መፍቻዎች
እነዚህን ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ መኖር አለበት፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል ዋጋም ሆነ በጥቅል ወይም በሎት መ/ቤቱ የሚያወዳድር መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማርኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 20 (ሃያ) ብር በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን 2% የሚውርስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር 8 ከተጠቀሱት ማስያዥያ ውጪ ያስያዘ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሁለት ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በማግስቱ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላችን በግ/ፋ/ን/አ/ቡድን መሪ ቢሮ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚከፍት ይሆናል።
- መ/ቤታችን ከሚገዛው እቃ 20% /ሃያ ፐርሰት/ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጨማሪ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 16 65 55 / 09 23 46 97 31 /09 88 82 40 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አመድ ጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን
