በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል ለሚገኙ ፅ/ቤቶች ለ 2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የእቃ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2017
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል ለሚገኙ ፅ/ቤቶች ለ 2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የእቃ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 3 የፅዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 4 የአቃቢ ህጎች የፕሮቶኮል ልብስ ግዥ
- ሎት 5 የመኪና ጎማ የመኪና ጌጣ ጌጥ እና ታፒሴሪ ስራ ግዥ
- ሎት 6 የ ደንብ ልብስ ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው::
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው
- ለሚወዳደሩባቸው የሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም-1 ሲፒኦ ለብቻ በታሽገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ከፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ሲያቀርቡ በካርቶን በደንብ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አሰ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 0115548264 /0118-69-43-66
በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
