Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ጤና ቢሮ የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ኮምቦልቻ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline26 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአብክመ ጤና ቢሮ ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ፣  ሎት 5 ህትመት እና ሎት 6 ፊክስድ ድጅታል ራዲዮግራፊ ማሽን አወዳድሮ ለአንድ አመት በሚቆይ ውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ጤና ቢሮ የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል


ብሔራዊ  ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

   የጨረታ  መለያ  ቁጥር  ኮጠሆ/ጨ/01/2017

በአብክመ ጤና ቢሮ ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ፣  ሎት 5 ህትመት እና ሎት 6 ፊክስድ ድጅታል ራዲዮግራፊ ማሽን አወዳድሮ ለአንድ አመት በሚቆይ ውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቲን ነምበር ያላቸው መረጃ ኦርጅናልና የማይመለስ ፎቶኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር መታሸግ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሞሉት ዋጋ ልክ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ኦርጅናሉን ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎታቸው ለብቻ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነ ቫቱ ነው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 103 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ 02/03/2017 ዓ/ም እስከ 17/03/17 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በእለቱ 4፡01 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  6. ሆስፒታሉ የጨረታ ውድድሩን አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር /በሎት ሲሆን ውድድሩ የሚካሄደው በየሎታቸው ለየብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም አሸናፊ ድርጅት እቃዎችን ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ከፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማምጣት አለበት፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም ተስተካክሎ በተጻፈው ትይዩ ፊት ለፊት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በፊርማ መረጋገጥ አለበት፡ ፡ ተጨማሪ መረጃዎችን በስልክ ቁጥር 0333510889 ደውለው ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 103 መጥተው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት እንዲሁም ውል በወሰደው እቃ ልክ 10% በባንክ የተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት ሳምፕል የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በተቀመጠው ሳምፕል መሰረት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ ተሳታፊዎች ዋጋ የሚሞሉት በኦሪጂናል ሰነድ ብቻ ነው እንዲሁም ተጫራቾች ዋጋ በሞሉበት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የህትመቱን ናሙና ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 103 በመምጣት ማየት ይችላሉ፡፡
  11. ሎት 6 የራዲግራፊ ማሽን ግዥ የሚፈጸመው በስፔስፊኬሽኑ መሰረት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የአንድ አመት ውል አይያዝም፡፡
  12. ጨረታው ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  13. ተጫራቾች የአማራ ክልል ላወጣቸው የግዥ መመሪያዎች ተገዥ መሆን አለባቸው፡ ፡ ማሸነፉ ከተገለጸ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  14. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በአብክመ  ጤና  ቢሮ  የኮምቦልቻ  ጠቅላላ  ሆስፒታል

Save Tender