በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክልል መንግስት ክህሎት ቴክኖሎጂ ቢሮ የቤንች ሸኮ ዞን የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውል እቃዎችና የተለያዩ ቋሚ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክልል መንግስት ክህሎት ቴክኖሎጂ ቢሮ የቤንች ሸኮ ዞን የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውል፡-
- የትምህርት አላቂ እቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት የሚውሉ አቃዎች
- የጋርመንት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- የእውቶሞቲቭ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- የጂሌም ኤፍ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- የኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- ለሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችና የተለያዩ ቋሚ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፤ የምዝገባ መለያ ቁጥር ያላቸው ፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ሲሆን፡-
- የጨረታ ማስከበርያ 20,000 /ሀያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የአንዱን ዲፓርትመንት ሰነድ 100 ብር በኢ/ን/ባንክ አካውንት ቁጥር 1000282806577 ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በመቁረጥ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቴክኒክና ሞያ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ያሸነፈውን እቃ ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ የሚችሉና ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማቅረቢያውን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ይሸጥና በ15 ተኛው ቀን ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ገብቶ ታሽጎ በማግስቱ ከቀኑ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።
- የጨረታ ቦታ አዲስ ከተማ ከፍለ / ቴ/ሙ/ ስልጠና ተቋም
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃዎች በውሉ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚሞሉት እቃዎች ዋጋ ቫትንና ትራንስፖርትን ያካተተ መሆን አለበት
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተገለጸ በኋላ አማን ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ መጥተው ውል መግባትና ያሸነፉትን እቃ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከገባ በኋላ በውሉ ላይ እስከተቀመጠበት ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ማሳሰቢያ ፡- ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር : 0473360271/0917827627/0932144862/0917390677
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ
