Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913247806
  • Website
  • Deadline25 Nov 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን መቀ/ገ/ወ/ፍ/ቤት ለመቤታችን አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሣሪያ የፅዳት እቃ ልዩ ልዩ እቃ ቋሚ እቃ ህትመት ደንብ ልብስ ለ2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን መቀ/ገ/ወ/ፍ/ቤት ለመቤታችን አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሣሪያ የፅዳት እቃ ልዩ ልዩ እቃ ቋሚ እቃ ህትመት ደንብ ልብስ ለ2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ተወዳዳሪዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከ200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ የሆኑ መወዳደር የሚችሉት የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች የሚወዳደሩ ሲሆን በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር / እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም መሥሪያ ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ 50 ብር /ሀምሳ ብር ብቻ ሰነዱን በመግዛት ግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ ፖስታውን የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ የምታስገቡ ሲሆን ጨረታው በአየር ላይ 15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን 15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

  • ለእያንዳንዱ የተዘጋጀ ሰነድ መሰረት ዋጋው መሞላት አለበት፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ሕጋዊና የዘርፉን ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የተሰረዘ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ የተከለከለ ነው፡፡
  • የግልጽ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆይበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው::
  • ተጫራቾች የሞሉት ሰነድ ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ለጨረታ የሚያስፈልገውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ያላቀረቡ ተጫራቾች በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ታክስን እና ጠቅላላ ዋጋ የሚያካትት/ የማያካትት መሆኑን በትከከል መገለፅ አለበት።
  • የጨረታ ሥርአቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያቸውን በመውረስ ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በሰሜን  ሸዋ  ዞን  የመንዝ  ቀያ  ገብርኤል  ወረዳ  ፍ/ቤት

Save Tender