በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በገ/ ጉ/ወ/ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የላብራቶሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ
ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/004/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በገ/ ጉ/ወ/ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የላብራቶሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጀቱ ባለቤት መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 50000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶከመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴከኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምት) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀከት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡
- የቦታው ምልከታ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው
- ተውዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅድመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራውን መስራት የሚችሉ መሆን ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልከ ቁጥር 0113360631/146 ይደውሉ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
