Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Dec 2024, 3:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው ካርጎ እና ሎጅስቲክስ ቅጥር ግቢ ውስጥ የእንስሳት ማቆያ ማዕከል ዲዛይን እና ግንባታ (Design & Construction of Live Animal Facility) ደረጃ ሶስት (3) ጠቅላላ ወይም ግንባታ ፈቃድ ያላቸውን ብቁ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ150 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር :- SSNT-T501

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው ካርጎ እና ሎጅስቲክስ ቅጥር ግቢ ውስጥ የእንስሳት ማቆያ ማዕከል ዲዛይን እና ግንባታ (Design & Construction of Live Animal Facility) ደረጃ ሶስት (3) ጠቅላላ ወይም ግንባታ ፈቃድ ያላቸውን ብቁ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ150 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. በአገልግሎት ዘርፉ ለ2015/2016 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና TIN ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብታት ማረጋገጫ ፈቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2015/16 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ ጠቅላላ ወይም ግንባታ ስራ ተቋራጭ የሆነ፡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  4. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰላሳ (30) ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T501 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሶስት መቶ ሺህ ብር (300,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለበት። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታህሳስ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል የጨረታ መክፈቻ ከፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ

 ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

 ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

አቶ አሊ አስፋው ስልክ ቁጥር፡ 011-5174552

ኢ-ሜል ፡ Ali As@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

Save Tender