የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም መሠረት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥን ለመፈጸም በRef Num-ET-MOUDI-Hawassa-415739-Go RFB Lot-3 (three) ድረስ ያሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም መሠረት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥን ለመፈጸም በRef Num-ET-MOUDI-Hawassa-415739-Go RFB Lot-3 (three) ድረስ ያሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ፡-
-
- INDUSTRIAL CONSTRCUTION MATERIALS Lot-03/2016
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አሥር ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ31ኛው ቀን 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ3፡45 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
