ስኬት ባንክ አ.ማ 2017 ዓ.ም በጀት የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ እና የተለያዩ መኪና ጎማዎች በሁለት ሎት ምድብ ንብረቶች/ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
Siket Bank (ስኬት ባንክ አ.ማ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ስኬት ባንክ አ.ማ 2017 ዓ.ም በጀት የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ እና የተለያዩ መኪና ጎማዎች በሁለት ሎት ምድብ ንብረቶች/ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የሥራ ሰዓት / ከሰኞ እስከ ቅዳሜ / ከባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የሥራ ቀን በባንኩ ዋ/መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 406 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እያንዳንዱ ሎት ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሁለቱንም ሎት መሠረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሁለቱም ሎት የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ለዕቃዎቹ ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚመልሱበት ጊዜ በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ልክ ናሙና /Sample/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ገጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ያልታሸገ ሰነድ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያስርዛል፡፡
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ይመለስላቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሰበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፈርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው መክፈቻው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመከፈቻው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በሚውልበት ቀን ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ሰዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ፊርማና ማህተም ማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
ምድብ ንብረት |
የሚገዛው የዕቃ ዓይነት |
CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ |
|
1 |
ሎት 1 |
የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ |
75,000 |
|
2 |
ሎት 2 |
የተለያዩ መኪና ጎማዎች ግዥ |
100,000 |
ማሳሰቢያ፡-
- አሸናፊ ተጫራቾች የግዥ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ ውል በመፈጸም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን ሎት ጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ከቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አንድ ላይ በማድረግ ከጨረታ ማስከበሪያውም ጋር በማሸግ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ ጋራንቲ ወይም በ CPO ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሁለቱንም ሎት የሚወዳደር ተጫራች ለሁለቱንም ሎት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለበት፡፡
- ባንኩ እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊት የሚገዙ ዕቃዎች መጠን 20% ለመጨመር/ሊቀንስ ይችላል፡፡
- የባንኩ የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2፡30 -11፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 1 11 15 12 /011 1 26 26 48 አዲስ አበባ፣
ስኬት ባንክ አ.ማ
