Tender Detail

Tender Details

  • Company ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና
  • Address ድሬዳዋ ከተማ፣ ገደንሰር ቀበሌ፣ ከድሬዳዋ ወደ ሁርሶ በሚወስደው መንገድ፣ ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ : ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251-252402380
  • Website
  • Deadline21 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የተለያዩ የግንባታ ተረፈ ምርቶች (Scrapy) እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና


ድሬዳዋ  ነፃ  የንግድ  ቀጠና  ያገለገሉ  ንብረቶች  ሽያጭ  ጨረታ

ማስታወቂያ  የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር - ድደነንቀ/ንማግጨ/01/2017

ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የተለያዩ የግንባታ ተረፈ ምርቶች (Scrapy) እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በማንኛውም ዘርፍ ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ድርጅት ወይም ማንኛውም ግለሰብ ።
  2. የጨረታውን ሰነድ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት የግንባታ ተረፈ ምርቶች እና ያገለገሉ ዕቃዎች መመልከት የሚፈልጉ ከጨረታው መክፈቻ ዕለት አስቀድሞ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ከድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስር የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ላይ በነፃ ንግድ ቀጠናው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሀንፃ አንደኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  5. የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ (Envelope) በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላውን የጨረታ ዋጋ 10% “በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና' ስም የተዘጋጀ ሲ.ፒ.አ ወይም ባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡ ፡ ከኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው በ 10 ቀናት ውስጥ የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
  8. ነፃ የንግድ ቀጠናው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ፡- ድሬዳዋ ከተማ፣ ገደንሰር ቀበሌ፣ ከድሬዳዋ ወደ ሁርሶ በሚወስደው መንገድ፣ ድሬዳዋ ነፃ

ንግድ ቀጠና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር :- 251-252402380 / 0921875123 / 09229063731

 

ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና

Save Tender