የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር በገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት እና በእቴጌ መነን አዳሪ ት/ቤቶች የሚውል አጠቃላይ የSTEM (የሳይንስ፣ ቴከኖሎጂ፣ ኢንጂነሪነግ እና የሂሳብ ማዕከል) ተከላ ፣ የእቃዎች አቅርቦት እና ማማከር ግዥ፤ ገጠማና ስልጠና ለመስጠት የወጣ ግዥ (Setting up STEM Education and Innovation Centers including Supply of Equipment & Devices and mentoring in Gelan Boys Boarding school and Etege Menen Girls Boarding School) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር በገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት እና በእቴጌ መነን አዳሪ ት/ቤቶች የሚውል አጠቃላይ የSTEM (የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪነግ እና የሂሳብ ማዕከል) ተከላ ፣ የእቃዎች አቅርቦት እና ማማከር ግዥ፤ ገጠማና ስልጠና ለመስጠት የወጣ ግዥ (Setting up STEM Education and Innovation Centers including Supply of Equipment & Devices and mentoring in Gelan Boys Boarding school and Etege Menen Girls Boarding School) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሱትን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ 200,000.00 ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከቢሮአችን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና ቢሮ ቁጥር 101 ሰነዱን በሶፍት ኮፒ፣ በኢሜል፣ ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦርጅናል ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ አስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ የመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት፣
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 122 64 56
አድራሻ፡- 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ
