Tender Detail

Tender Details

  • Company የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
  • Address አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 261365
  • Website
  • Deadline19 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአራት ኪሎ ስፖርት፡ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት መሳሪያዎች: የደንብ ልብስ፣ የዕዳት ልቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የምግብ ዕቃዎች እና የምግብ ግብዓቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል


የግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

(01/2017) ዓ.ም

የአራት ኪሎ ስፖርት፡ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት መሳሪያዎች: የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ልቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የምግብ ዕቃዎች እና የምግብ ግብዓቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተዘረዘሩትን  መስፈርቶችን  ማሟላት  አለባቸው፡፡

  1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ።
  2. ተጫራቶች በሙሉ ሆነ በከፈል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ለሚመለከተው እካልም በደብዳቤ ይገልፃል፡፡
  3. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት::
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መግለፅ አለበት።
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ - ከአራት ኪሎ ስፖ/ትም/ስል ማዕከል የፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይቻላል።
  6. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስር የስራ ቀናት ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 ይከፈታል በማግስቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቶች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ በታሸነ ኤንቨሎፕ አሪጅናልና ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንስና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባችኋል።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  9. ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ /ዶክመንት አንቀበልም ::
  10. ለአሸናፊዎቹ ከፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን ዕቃ በተጠየቀውና ባሸነፈው ናሙና መሰረት ሙሉ በሙሉ ገቢ ከተደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን
  11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  12. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃዎችን ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ላሸነፉት ዕቃ ለማቅረብ የውል ስምምነት ይፈርማል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  15. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለስፖርት ትጥቅ ሲፒኦ CPO ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል እና ለደንብ ልብስ፤ ለፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የምግብ ዕቃዎች እና የምግብ ግብዓቶች ሲፒኦ /CPO ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ:- አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ ለበለጠ መረጃ ስልክ 011 1 261365/ 011 1 23 35 33

 

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል

Save Tender