የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለጥገና ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል - ሎት-1 የጽዳት ዕቃ እና ሎት 2 ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለጥገና ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል - ሎት-1 የጽዳት ዕቃ እና ሎት 2 ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) ማቅረብ ሚችሉ
- የግዥ መጠን 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፍቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ/ፋይ/ከገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲኦፒ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሠነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 19 ግዥ/ፋይ/ንብ/ አስተ/ደ/የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ከ29/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 14/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በ 14/03/2017 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
- አሸናፊ የሚለየው ሎት-1 የጽዳት እቃ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት) ሲሆን ሎት-2 ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ ዕቃዎች በነጠላ ዋጋ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተ/ደ/የስራ ሂደት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0588910823 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጐጃም ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት
ደ/ማርቆስ
