የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እስቴሽነሪና /የጽህፈት መሳሪያ/ እና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ጎፋ ክላስተር ሳውላ
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እስቴሽነሪና /የጽህፈት መሳሪያ/ እና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ብር 10000 /አስር ሺ ብር/ ለእስቴሽነሪ 5000.00 /አምስት ሺ ብር/ ለጽዳት እቃዎች / በቢሮአችን ስም በተዘጋጀና በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮአችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው:: ሳጥኑም በ15ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ከ15 የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቢሮአችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሮአችን መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ቢሮአችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጮች ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክቁጥር 0920324072/0911914247
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ
ጎፋ ክላስተር ሳውላ
