Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ጎፋ ክላስተር ሳውላ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0920324072
  • Website
  • Deadline22 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Computers

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ላፕቶፕ ኮምፒውተርና ታብሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ጎፋ ክላስተር ሳውላ


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ላፕቶፕ ኮምፒውተርና ታብሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለ መመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው፤
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10000 /አስር ሺ ብር /በቢሮአችን ስም በተዘጋጀና በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድ ቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።
  5. ተጫራቾች በኢትዮጵያን ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮአችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ሳጥኑም በ15ኛው ቀን በ11:00 ሰዓት ይታሸጋል።
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቢሮአችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  8. የጨረታው አሸናፊ እንደ ታወቀ የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ ላላሸነፉት ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለሳል።
  9. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሮአች መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት። ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  10. በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሰረት ይስተናገዳሉ።
  11. ቢሮአችን ጨረታውን አስመልከቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁጥር  0920324072/0911914247

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ

ጎፋ ክላስተር ሳውላ

Save Tender