በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሸ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግሸ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4 የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት5. የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፣ ሎት 6. የመኪናና የጀነሬተር ባትሪዎች፣ ሎት7 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ሎት8. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 9 አሸዋ ፣ ሎት 10 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 11 ጫማዎች፣ ሎት 12 ፕላስቲክ ቦት ጫማዎች፣ ሎት 13 ብትን ጨርቅ በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሸ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሸ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግሸ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4 የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት 5. የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፣ ሎት 6. የመኪናና የጀነሬተር ባትሪዎች፣ ሎት7 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ሎት 8. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 9 አሸዋ ፣ ሎት 10 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 11 ጫማዎች፣ ሎት 12 ፕላስቲክ ቦት ጫማዎች፣ ሎት 13 ብትን ጨርቅ በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው/ያላት፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /የቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ሎት የጽሕፈት መሣሪያ በብር 100፣ ሎት2. የጽዳት እቃዎች ብር 80፣ ሎት3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ብር 30፣ ሎት4 የኮፒውተርና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ብር 80፣ ሎት5. የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ብር 80፣ ሎት6. የመኪናና የጀነሬተር ባትሪዎች ብር 30፣ ሎት7 ቋሚ አላቂ እቃዎች ብር 50፣ ሎት8. የኮንስትራክሸን ማቴሪያሎች ብር 100፣ ሎት 9 አሸዋ በብር 50፣ ሎት 10 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች ብር 50፣ ሎት 11 ጫማዎች ብር 40፣ ሎት 12 ፕላስቲክ ቦት ጫማዎች ብር 30፣ ሎት 13 ብትን ጨርቅ ብር 40 በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በኢትዮጵያ ብሔራው ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of credit ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ለየብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ለተጫረቱበት ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ሲያሲዙ በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን በመሙላት ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 06 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሎት /በጥቅል ድምር/ መሆኑ ይታወቅ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0331191314 /0338990102 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ከላይ ያልተገለጸ ካለ በመመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሕዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
በሰ/ሸዋ ዞን የግሰ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
