በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ፤ እንጦጦ ጫንጮ ፤ በረክ ፤ እና ምስራቅ ሸዋ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OFWE/BA-01/2017
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ፤ እንጦጦ ጫንጮ ፤ በረክ ፤ እና ምስራቅ ሸዋ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የጊንድላ ፣ የአጣና ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ አና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸዉ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታዉ የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር አንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ/ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡-
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡ በስልከ ቁጥር 0111240249 መደወል ይችላሉ
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
