የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካልና አፓራተስ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው የኬሚካሎች እና የአፓራተስ ዓይነትና ብዛት መሠረት በአራት ሎት ተከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ ብቃት ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB/OEB/GOV/02/2017
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካልና አፓራተስ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው የኬሚካሎች እና የአፓራተስ ዓይነትና ብዛት መሠረት በአራት ሎት ተከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ ብቃት ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ሎት አንድ ኬሚካሎች፣
2. ሎት ሁለት የባዮሎጅ አፓራተስ፤
3. ሎት ሦስት የኬሚስትሪ አፓራተስ፣
4. ሎት አራት የፊዚክስ አፓራተስ፣
በዚሁ መሠረት፡- ከላይ በሎት የተከፋፈሉት ኬሚካሎች እና አፓራተሶችን ማለትም በሎት 1-4 ከተዘረዘሩት ሎቶች ውስጥ በተወዳደሩበት "Item` አንዱን ዕቃ ማስቀረት በፍጹም የተከለከለ ነው።
ስለሆነም ተጫራቾች በተሠረቱበት እያንዳንዱን ሎት በየሎቶቹ መጠይቅ መሰረት ለየብቻ ተለይቶ በፖስታ በማሸግ ለመጫረት በማቅረብ ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ እቃዎቹን ገላን በሚገኘው ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ንብረት ክፍል ማድረስ የሚችሉ ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ጋር፡-
- በዘመኑ ታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያሰችል ደብዳቤ (Clearance))፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ (Bid Bond) ወይም CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ (Un conditional Bank Guarantee) በየሎቱ ለየብቻ ለየብቻ በእያንዳንዱ የሎቱ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር 0.5% በኦሮሚያ ት/ቢሮ (To Oromia Education Brueau) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለበት፡፡ ይሁንና የጨረታው ማስከበሪያ ከ5000,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ መሆን የለበትም::
- ተጫራቶች ኬሚካሎቹን/ አፓራተሶቹን ዝርዝር ነጠላ ዋጋ እና ካሻት ጋር ከጨረታው ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔሰፊኬሽን መሠረት በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገፆች ላይ በማሳረፍ ከ1-4 የተዘረዘሩትን እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በመሙላት ፋይናንሻል ኦሪጂናል፣ ቴክኒካል ኦሪጂናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ ፣ቴክኒካል ኮፒ እና CPO ለእያንዳንዱ ለየብቻ ለየብቻ በፖስታ ከተሸነ በኋላ ለእያንዳንዱ ሎት በአንድ ላይ ፖስታ ታሽጎ ከሳር ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን ፦ ስልክ ቁጥራቸውንና የጨረታ ቁጥሩን በፖስታ ላይ በመጥቀስ የጨረታ ማሰታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን በማስገባት 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን እስከ 4:00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ወይንም አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ስ.ቁ 0113717973
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
