የጎንደር ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት ወረቀቶች፣ የህትመት፤ ጥሬ እቃዎች እና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደር ማተሚያ ድርጅት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት ወረቀቶች፣ የህትመት፤ ጥሬ እቃዎች እና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪ ድርጅት ያገለገሉ ጅቲኦ 52 የህትመት ማሽኖችን፣ የወረቀት መቁረጫ እና የሽቦ መስሪያ ማሸኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቃል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የምችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች ጠቃሚ ናቸው የሚሏቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አዲስ አበባ ላለው ግዥ ሠራተኛ በስልክ ቁጥር 0911204902/0918082215 በመደወል ወይም ጎንደር ማተሚያ ድርጅት ዋናው መ/ቤት መላክ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የገንዘብ መጠን ወይም ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ይህ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ21ኛው ቀን ከቀነ 7፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ በጎንደር ማተሚያ ድርጅት በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይፈፀማል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪውን ስም አድራሻ የሚመለከት /ህጋዊ/ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ ከድርጅቱ አቅርቦትን ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581-11-16-72 ወይም በስልከ ቁጥር 09-11-20-49-02 ወይም 058-211-94-95 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከአዲስ አበባ ግዥ ሰራተኛ ወይም ከዋናው መ/ ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደር ማተሚያ ድርጅት
