የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Prosperity Party (የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት)
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-01/2017
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፤
ሎት 2 የፅዳት ዕቃ፤
ሎት 3 ደንብ ልብስ፤
ሎት 4 የመኪና ጌጣጌጥ፤
ሎት 5 የቧንቧና የሳኒቴሽን ዕቃዎች፤
ሎት 6 ኤሌክትሮኒከስ፤
ሎት 7 የአይሲቲ ዕቃዎች
- ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ያላቸው፣
- በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 / ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል አራት ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-02 በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሎት 7. 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በ ሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለበት የባንክ ዋስትና ብቻ በብልፅግና ፓርቲ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከሁለቱ አማራጮች ውጭ የሚቀርብ ማስያዣ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል፡፡ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ የአንዱን ዋጋ፣ ጠቅላላ ዋጋ እና ቫትን አካቶ ያለውን ድምር በመጨመር ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒውን እንዲሁም ሲ.ፒ.ኦ በተለያያ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-24-34-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት
