Tender Detail

Tender Details

  • Company የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ይ/ዓለም ከተማ : ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline27 Nov 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽ/ቤት በኩል በመደበኛ Procurement Reference Number: YIRGALEM stadium Maintenance andnewwork/CW-02/በ02 ቀበሌ የይ/ዓለም ከተማ አስተዳደር ሁለገብ ስታዲየም የጥገናና አዲስ ግንባታ ስራ ፕሮጀክት ለማስገንባት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን ደረጃ 5-GC ብቻ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽ/ቤት በኩል በመደበኛ Procurement Reference Number: YIRGALEM stadium Maintenance andnewwork/CW-02/በ02 ቀበሌ የይ/ዓለም ከተማ አስተዳደር ሁለገብ ስታዲየም የጥገናና አዲስ ግንባታ ስራ ፕሮጀክት ለማስገንባት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን ደረጃ 5-GC ብቻ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ደረጃ 5-GC ብቻ ፈቃድ ያላቸው
  2. የኮንስትራክሽን ስራ የ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የዘመኑን የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ከሲ/ብ/ክ/መንግስት ከክልል ቢሮ እና ከፌዴራል ን/አ/ባለስልጣን ብቻ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  7. በይ/ዓለም ከተማ አስተዳደር የግንባታ ስራ ወስደው 100% ያላጠናቀቁ ኮንትራክተሮች ጨረታውን መወዳደርም ሆነ ሰነዱን መግዛት አይችሉም፡፡
  8. በይ/ዓለም ከተማ አስተዳደር ውስጥ ፕሮጀከቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር ከ2014 ጀምሮ ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛውም ዓይነት የስራ አፈጻጸም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
  9. የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ/ የተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ bid security unconditional guarantee 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ቫት የተመዘገቡበትን ሴርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለሃያ አንድ /21/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ግዥ ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ በተቋራጮች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ /bid security, bid Submission sheet/ ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 22ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ብቻ በይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  12. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ 2% በላይ ከሆነ ከጨረታ ወድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  13. በጨረታው ላይ ካለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር /10/ ፐርሰንት በላይ የዋጋ ቅናሽ / REBATE/ የተደረገ ከሆነ ቀጥታ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
  14. በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከመሃንዲስ ግምት /ከወቅቱ የገበያ ዋጋ በፐርሰንት 15% በላይ ካቀረቡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቀጥታ ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ፤
  15. በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከመሃንዲስ ግምት /ከወቅቱ የገበያ ዋጋ በፐርሰንት 15% በታች ካቀረበ የወቅቱ የገበያ መዋዠቅ እና የስራውን አንገብጋቢነት በማስቀደም ኮስት ብሬክዳውን /cost break down/ እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡
  16. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡
  17. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ነው፡፡

 

የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender