Tender Detail

Tender Details

  • Company የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251124968
  • Website
  • Deadline21 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Medical Equipment And Supplies

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉና ለማህበረሰብ ፋርማሲ ሎት 1. የመድሃኒትና የህከምና መገልገያ መሳሪያዎች ሎት 2. ኦከሲጅን ሎት 3. አንሶላ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊና ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ


የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ድ/ዳ/ሣ/ጠ/ሆ 5/2017

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉና ለማህበረሰብ ፋርማሲ ሎት 1. የመድሃኒትና የህከምና መገልገያ መሳሪያዎች ሎት 2. ኦከሲጅን ሎት 3. አንሶላ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊና ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለሰ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቁጥር 3 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንከ የተመሰከረለት ቼክ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።  ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን ውል ማከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0251124968 /0912058798 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ

Save Tender