Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address አርሲ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0223311521
  • Website
  • Deadline20 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአርሲ ዞን ከፍ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁ-03/2017

የአርሲ ዞን ከፍ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና በፈዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ፈርኒቸር ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ለጽዳት እቃዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) በአርሲ ዞን/ ከ/ ፍ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000022906961 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15ተከታታይ የሥራ ቀናት በአርሲ ዞን/ ከ/ ፍ/ቤት የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 31 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ፈርኒቸር የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ)፤ ለጽዳት እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንከ በክፍያ ማዘዣ (C.P.0.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  1. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የዞኑ/ከ/ ፍ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  2. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0223311521,0913382845,0913819026 ይጠይቁ፡፡

 

የአርሲ ዞን ከ/ፍ/ቤት

Save Tender